ስለ ጥበብ ቤተሰብ

እኛ ቤተሰባዊ መስተጋብር በተመለከት አዲስ እይታን ለማምጣት እና የቀጣዩን ትውልድ መሪዎች ለማጎልበት ዓለም አቀፍ ንቅናቄ ለመቀስቀስ ጥልቅ ፍላጎት ያለን የመምህራን፣ የፈጠራ ሰዎች እና የማህበራዊ ፈጠራ ባለሙያዎች ቡድን ነን። በተረት ነገራ ኃይል እና መሳጭ በሆነ ትምህርት አማካኝነት፣ በወላጆች እና በልጆች መካከል ትስስርን እናጠናክራለን፣ በዚህም የሰውን ልጅ ትልልቅ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ዝግጁ የሆኑ፣ ርህሩህነት ያላቸው የለውጥ አራማጆችን እንኮተኩታለን። 

ተልዕኮአችን

የቤተሰብ ግንኙነቶችን ማጠናከር እና ወላጆች እና ልጆች በቤቶቻቸው፣ በማህበረሰቦቻቸው እና በዓለም ላይ አዎንታዊ ማህበራዊ ለውጥ እንዲፈጥሩ ማበረታታት። 

ራዕያችን 

ቤተሰቦች እንደ አድሎኛነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ማህበራዊ ኢፍትሃዊነት ያሉ ጉዳዮችን ለመጋፈጥ የታጠቁ፣ ባህላዊ እውቀትም ዓለም አቀፍ እይታም ያላቸው በጥብቅ የተሣሠሩ ስብስቦች ማስቻል።

አቀራረባችን 

በጥበብ ቤተሰብ ውስጥ የተሻለ ዓለምን ለመፍጠር ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር የመሠረት ድንጋይ ነው የሚል መሠረታዊ እምነት አልን። ወላጆች እና ልጆች ነጻ በሆነ ተግባቦት (የሐሳብ ልውውጥ)፣ አንዱ ሌላውን መረዳት በመቻል፣ እና ልምዶችን በመጋራት በጥልቅ ደረጃ ትሥሥር መፍጠር ሲችሉ ምንም የማያቆማቸው የመልካምነት ኃይሎች ይሆናሉ።

ይህ ዋና ፍልስፍና፣ ቤተሰቦችን በትረካ፣ በሚያሳትፉ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎች እና በእውነተኛ-ዓለም ጉዳዮች ላይ በመወያየት እንዲቀራረቡ የሚያስችለው ትምህርታዊ አቀራረባችንን መሠረት ነው። የእኛ በተግባር ውጤታማነቱ የተረጋገጠው ባለ3-ምሰሶ ሞዴል በአንድ ጊዜ ትሥሥርን ያጠናክራል በዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች ላይ አመለካከቶችን ያሰፋል አዎንታዊ አካባቢያዊ ተፅእኖን በሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች ላይ የትብብር እርምጃንም ያነሳሳል።

ሥረ-መሠረታችን፦ ፈር ቀዳጁ የጥበብ ልጆች አጽናፈ-ዓለም

የጥበብ ቤተሰብ የተወለደው ከፋና ወጊው የጥበብ ልጆች አጽናፈ-ዓለም ነው። የህም፣ በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የልዕለ ኃያል ገጸባህሪያት ታሪኮችን እና የትምህርት ሚዲያን በበየነ=አህጉራዊ ትብብር እውን አድርጓል። በባለራዕይዋ ፈጣሪ በብሩክታዊት ጥጋቡ የተፀነሰው የጥበብ ልጆች ሽልማት አሸናፊ የሆነው የዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ ያዘጋጀው ነው።

ዊዝ ኪድስ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ለኢትዮጵያ ልጆች እና ቤተሰቦች ትምህርት እየቀየረ ያለ ፈር ቀዳጅ ማህበራዊ ድርጅት ነው። ዊዝ ኪድስ ከ10 የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ የተውጣጡ ልዩ የፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ሰዎች በአንድ ላይ በማምጣት የባህል ኩራትን እና የዕድሜ ልክ የመማር ፍቅርን የሚያነቃቁ የጥበብ ልጆችን መሳጭ ዓለማት ፈጥሯል። 

የዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ የቤተሰብ የጋራ ልምምድን ኃይል በመገንዘብ፣ ለዋጭ እድገትን እና የአቅም ማጎልበት ጥረትን በቤተሰብ ስብስብ በራሱ ውስጥ ለማኖር የጥበብ ቤተሰብን ፈጠሯል። ይህ ተፈጥሯዊ የለውጥ ሂደት የጥበብ ልጆች አጽናፈ ዓለም በወላጆች እና በልጆች መካከል ትርጉም ያለው ውይይቶችን በማቀጣጠል ሙሉ ክበብ እንዲፈጥር ያደርገዋል። 

የዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ ዘላቂ ተፅእኖ

በእያንዳንዱን ስርጭት ወቅት ከ10,000,000 በላይ ልጆችን እና ቤተሰቦችን ይደርሳል።

በ7 የአከባቢ ቋንቋዎች ከ25 በላይ ማሰራጫ አጋሮች አሉት።

ከ200,000 በላይ በትምህርት ላይ ያሉ ልጆች ተጠቃሚ ያደርጋል።

ንቅናቄአችንን ይቀላቀሉ

እርስዎ የምወክሉት ፋውንዴሽንን፣ ኮርፖሬሽንን፣ ትምህርት ቤትን ወይም የፈጠራ ችሎታ ያለው ግለሰብን ቢሆኑም፣ የአጋርነት ዕድሎችን እንድመረምሩ እና በትምህርት እና በቤተሰብ ትስስር ግንኙነት ላይ ያለውን እይታ እንደገና ለመበየን በምናደርገው ጥረት ውስጥ እንድደግፉን እንጋብዝዎታለን።

  • ፋውንዴሽኖች እና ኮርፖሬሽኖች

    የእርስዎ ድጋፍ አሳታፊና በይነተገናኝ ኮርሶቻችንን ለሁሉም ቤተሰቦች ፍትሃዊ የወደፊት ሕይወትን በሚፈጥሩ የተቀናጀ የመማሪያ ሞዴሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ ያስችለናል።

  • ትምህርት ቤቶች እና አስተማሪዎች

    በትረካ ለዋጭ ኃይል የሚመሩትን በፈጠራ የተሞሉ የማህበራዊ እና ስሜታዊ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርታችንን በመማሪያ ክፍሎችዎ ውስጥ በማስገባት የማወቅ ጉጉትን ያቀጣጥሉ፣ በቤት እና በትምህርት ቤት መካከል ያለውን ትሥሥርም ያጠናክሩ። 

  • የፈጠራ ሰዎች እና አርቲስቶች

    ውቅረ-ልቦናን መቀየር የሚችሉና ባህላችንን የሚያንጸባርቁ ተረቶች አጽናፈ ዓለማችንን ለማስፋት እንዲተባበሩ ሁልጊዜም ልዩ ብቃት ያላቸው ጸሐፊዎችን፣ ሰዓሊያንን፣ አኒሜተሮችን እና ዲዛይነሮችን እንፈልጋለን።

ሽልማቶቻችን

የዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ በትምህርትና በልጆች ሚዲያ ውስጥ ለሠራናቸው ፈር-ቀዳጅ ሥራዎቻችን ዓለም አቀፍ አድናቆትን አግኝቷል፣ ከ10 በላይ ታዋቂ ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል።

አጋሮቻችን

ያለፉት እና የአሁን አጋሮቻችን ተደራሽነታችንን እና ተፅእኖአችንን ለማጎልበት፣ የቤተሰብ ትስስርን ለማጠናከር እና አዎንታዊ ማህበራዊ ለውጥን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሳካት ተልዕኳችን ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።