እንኳን ወደ የወጣት ስራ ፈጣሪዎች የእንግሊዝኛ ትምህርት በደህና መጣችሁ! | እንኳን ወደ የወጣት ስራ ፈጣሪዎች የእንግሊዝኛ ትምህርት በደህና መጣችሁ! እንኳን ወደ የወጣት ስራ ፈጣሪዎች የእንግሊዝኛ ትምህርት በደህና መጣችሁ!

ወጣት ስራ ፈጠራዎች በዋናነት ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን  ችግሮች ለመፍታት በሚያግዙ ክህሎቶች ዙሪያ በተነሳሽነት ተግቶ በመስራት ለእናንተ ለወጣቶች በሚመች መልኩ ስራን ለመፍጠር የሚያግዙ ተግባራዊ ኮርሶችን የሚያቀርብ ነው። ስለሆነም የቋንቋ ትምህርት በተለይም በእንግሊዝኛ የቋንቋ ዘርፍ ጠንክረን በመስራት ልዩ እና ውጤታማ የሆነ ትምህርትን አስደሳች እና አዝናኝ በሆነ መንገድ ለሁሉም ወጣቶች በማቅረብ፣ እንግሊዝኛን ልክ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋችው እንዲግባቡበት እና በጣም የተወሳሰቡ ሃሳቦች በቀላሉ እንዲገልጹ በሚያስችሉ የቋንቋ አቀራርቦች ላይ ትኩረት ሰጠን እንሰራለን።  በእውነተኛ የዕለት ተዕለት ህይወታዊ ሁኔታዎች ላይ በማተኮር የሰዋስው፣ የቃላት አነጋገር እና የቃላት ድምጸት እና አጠራርን ጨምሮ ሁሉንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ መሰረታዊ ነገሮች ላይ በዋናነት እናተኩራለን።

ተልዕኳችን

እንግሊዝኛ ቋንቋ እንደመሆኑ መጠን በአብዛኛዎቹ አገሮች ውስጥ ለመስራት እና መረጃን ለማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው።  
ስለሆነም የእኛ ዋና ተልዕኳችን፦
  • እንግሊዝኛ ቋንቋ ለስራ ፈጠራ እንቅፋት መሆኑን ማስቀረት: ሃሳብን እና እዉቀትን ቋንቋ ሳይገድበው ወይም እንቅፋት ሳይሆን  ከዓለም አቀፋዊ ማኅበረሰብ ጋር ሃሳብን በመለዋወጥ የፈጠራን ችሎታ እንዲያዳብሩ መርዳት።
  • አፍ መፍቻ ቋንቋችው እንግሊዘኛ እንደሆኑ ተወላጆች አቀላጥፈው እንዲናገሩ እና በጣም የተወሳሰቡ ሃሳቦችዎን እንኳን በቀላሉ እንዲገልጹ እና እንዲገነዘቡ መርዳት።
  • እንግሊዝኛ ቋንቋ ለዕዉቀት እና መረጃ:- ቋንቋ ለፈጠራ እንቅፋት የሚሆንበትን መንገድ በመቅረፍ ሁሉም የሃገራችን ስራ ፈጣሪ ወጣቶች መረጃን በተገቢው መንገድ አደራጅተው ያላቸዉን ልዩ ሃቅም ለስራ ፈጠራነት እንዲጠቀሙ ማስቻል።

 ራዕይ

  • እንግሊዝኛ ቋንቋ ለስራ ፈጠራ እንቅፋት መሆኑን በማስቀረት በኢትዮጵያ በቀዳሚነት የፈጠራ ስራን ማበረታታት።

ልዩ የሚያደርገን ምንድን ነው?


  • ተደራሽነት፡ ቋንቋን መማር ለሚፈልግ ሁሉ  ቦታን፣ ጊዜን፣ጾታን እና ማንነትን ሳይለይ በቁርተኝነት ተደራሽ ማድረግ መቻላችን።
  • ሳይንሳዊ ዘዴ መከተላችን፦ እየተዝናኑ እና እየተደሰቱ እንዲማሩበት አድርገን ማዘጋጀታችን እና  እንደ “Pimsleur” ባሉ  በዓለም ላይ በተረጋገጡ ቋንቋን የማስተማሪያ ዘዴዎች በመጠቀም  ትምህርቶች ማዘጋጀታችን።
  • የዕለት ከዕለት የህይወት እንቅስቃሴዎች ጋር አያይዘን ማቅረባችን፡- የዕለት ከዕለት ውይይቶች፣ስራን፣ እንቅስቃሴን እና ሙያዊ ስኬትን ለማዳበር በሚረዱ የቋንቋ ዘርፎች ማካተታችን።
  • ተለዋዋጭነት፡- በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ፣ ከተማሪዎች የአኗኗር ዘይቤ ጋር በሚስማማ መልኩ ተዘጋጅቶ መቅረቡ።

 Other Projects

Our mission is to empower learners with the skills they need to thrive in an interconnected world.

Develop your professional skills

Boost your confidence, master the field, become a certified professional

Become a learner every day

We will help you unlock your inner potential, so you can excel in your professional field.

Learn Easier, Anytime & Anywhere

Learn to use all the related tools, walk into a job and be a rock star from day one

ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ

ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ እ.ኤ.አ በ 2005 የተቋቋመ ሀገር በቀል ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ሲሆን የልጆች፣ የታዳጊዎችን እና የወጣቶችን ህይወት ለማሻሻል ይሰራል። ዊዝ ኪድስ ዘላቂ የሆነ የባህሪ እና ማህበረሰባዊ ለውጦች ለማምጣት እድሜን፣ ቋንቋን፣ ባህልን እና የእድገት ደረጃን ያማከሉ በጥናት የተደገፉ የፈጠራ ስራዎችን ቴሌቪዥን፣ ራዲዮን እና በይነ መረብ/ኢንተርኔት፣ ት/ቤቶችን፣ ፌስቲቫሎች እና ማህበረሰባዊ ስብሰባዎችን ተጠቅሞ በማሰራጨት ከ 10 ሚሊየን በላይ ህፃናትን፣ ታዳጊዎችን እና ቤተሠቦቻቸውን እያገለገለ ይገኛል። ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ ለሀገር እያደረገ ባለው መልካም አስተዋጽኦ በርካታ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ ላሉ ህፃናት/ልጆችን እና ወጣቶችን ለመደገፍ ፀሐይ ለቤተሰብ፣ ፀሐይ መማር ትወዳለች፣ የጥበብ ልጆች እና ወጣት ፈጣሪዎች /ተመራማሪዎች የሚሉትን አራት የፈጠራ ስራዎች /ኢኖቬሽኖች ይጠቀማል።
Created with