Jul 27 / ብሩክቲ

ከልጅዎ ጋር አብሮ በመዘመር የተረጋጋ ባህሪን መፍጠር

ከልጅዎ ጋር አብሮ በመዘመር የተረጋጋ ባህሪን መፍጠር

ለመጨረሻ ጊዜ ትንሹ ልጅዎን ሲያለቅስ የሰሙበትን ቅፅበትን ያስታውሳሉ? ልጅዎን ለማስታገስ ምን አደረጉ? ልክ እንደ አብዛኞቹ ወላጆች ከሆኑ ልጆችዎን ለመመገብ፣ ለማባበል፣ ልጅዎ እንዲያገሳ ለማድረግ፣ ለማዘናጋት እና “እሽሩሩ” ማለትን ሞክረው ይሆናል። ሞክረዋል አይደል? ከተዘረዘሩት አንዳቸውን ለመሥራት ምን ያህል ጊዜ ወሰደብዎት?

እነዚህ ቴክኒኮች ጥሩ ሊሆኑ ይችላሉ ቢሆንም ግን ልጅዎን ለማረጋጋት ሌላ መጠቀም ያለቦት በጣም ጠቃሚ እና አዝናኝ መላ አለ።እሱም፡
ሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው የህጻናት መዝሞሮችን መዘመር ህፃናት እንዳያለቅሱ ለማድረግ እሽሩሩ ከማለት እና እነሱን ከማቀፍ ይልቅ በጣም ውጤታማ ሊሆን ይችላል! እንደሚችል ያስቀምጣል።
የመዝሙር ተፅዕኖዎች እንደ እውነቱ ከሆነ ህጻናት መዝሙር በሚያዳምጡበት ጊዜ (ከዚህ ቀደም የማያውቁት ቢሆንም) ንግግርን ከሚያዳምጡበት ጊዜ ይበልጥ (የህፃን ልጅ ንግግር ቢሆንም ባይሆንም) ረዘም ላለ ጊዜ ተረጋግተው ይቆያሉ። እነዚህ ግኝቶች በጣም አስፈላጊ ናቸው። ምክንያቱም ብዙ እናቶች ለልጆቻቸው ከመዘመር ይልቅ ብዙ ጊዜ ንግግርን ያበዛሉ።
ልጅዎን ለማረጋጋት ምን ዓይነት መዝሙሮችን መዘመር ይችላሉ?
ጥናቶች ህጻናት በጣም ረጋ ላሉ መዝሙሮች እና ጩኸት ለበዛበት መዝሙር ምን ምላሽ እንደሚሰጡ ለማነፃፀር ሞክረዋል። እናም ረጋ ያሉ መዝሙሮች ህፃናትን ለማረጋጋት እንዲሁም ለማዝናናት የሚረዱ ጠቃሚ የመዝሙር አይነቶች እንደሆኑ በበጥናት ተረጋግጧል። በተጨማሪም የእነዚህ ልዩ መዝሙሮች ዜማ ህጻናትን ዘና ለማድረግ እንደሚረዳም ጠቅሰዋል። ምንም እንኳን ጩኸት የበዛባቸው መዝሙሮችም አሪፍ ቢሆኑም ረጋ ያሉ መዝሙሮች ህፃናትን መማረጋጋት ወደር የለሽ ናቸው።
ስለዚህ ለመዘመር ድምፄ በጣም ጥሩ አይደለም ብለው ቢያስቡም ግድ የለም! ድምፅዎ አማረም አላማረም እንደ እውነቱ ከሆነ ልጅዎ ድምጽዎን በጣም ይወደዋል። እንዲሁም ከእርስዎ የመዝሙር ፈለግ በመከተል ከእርስዎ ጋር የመቆራኘት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል። ለልጅዎ መዘመር የሚያስገኘው ጥቅም ከማንኛውም ደህንነት ካለመሰማት እና አለመተማመን የበለጠ መሆን አለበት። በመዘመር ልጅዎን ማስታገስ ብቻ ሳይሆን በሁለታችሁም መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር እና የቋንቋ ችሎታቸውን ለማሳደግ እንደሚያግዟቸው ያስታውሱ!
ረጋ ያሉ መዝሙሮች የልጅዎን ራስን የመቆጣጠር ችሎታ እንዲያጎለብቱ ሊረዷቸው ይችላሉ። ትንንሽ ልጆቻችሁን በምታዝናኑበት ጊዜ ስሜታዊ ሁኔታቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን ለማስተዳደር የሚረዱ ክህሎቶች እንዲሁም ራሳቸውን ለማስታገስ የሚጠቅሙ ችሎታዎችን ያሳድጋሉ። እንዲሁም በዘፈን ምት በመደነስ እና ሙዚቃው ሲቆም ዝም ብለው በመቆም የልጅዎ ራስን የመቆጣጠር ችሎታ ማዳበር ይችላሉ። አብሮ መዘመር ትንንሽ ልጆቻችሁ በራስ የመተማመን ስሜታቸውን እና ለራሳቸው ያላቸውን ግምት እንዲያሳድጉ እድል ይሰጣቸዋል። ከእነሱ ጋር ስትዘምሩ የዓይንን ግንኙነት ለመጠበቅ እና በመዝሙሮቹ ውስጥ ስማቸውን ለመጠቀም ይሞክሩ። የትኞቹ ዘፈኖች እና ዜማዎች በጣም የሚዝናኑ እንደሚመስሉ ልብ ይበሉ። መዝሙር የልጆችን ግልፍተኛ ባህሪን ለመቀነስ ስለሆነም መዝሙር ወይም ሙዚቃ ልጆች ግልፍተኛ ባህርያቸውን ለመቆጣጠር ከሚወሰዱ አማራጮች አንዱ ነው። በዚህ ዙርያ የተደረጉ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሙዚቃ በስሜት እፎይታ በኩል ስሜቶችን የመቆጣጠር ፍላጎትን በተለይም ግልፍተኛነትን እና ቁጣን ለማሻሻል እድሎችን ይሰጣል።
ሙዚቃ ግልፍተኛ ባህሪን እንደሚቀንስ እና ከፍተኛ ግልፍተኛ ባህሪ ባላቸው ህፃናት ላይ ለራሳቸው ያላቸውን ግምት እንደሚያሻሽል ብዙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። መዝሙር ለልጆች በቀላሉ ተደራሽ ሊሆን የሚችል ሕክምና ሲሆን በተጨማሪም ግልፍተኛ ባህሪን ለመግራት ውጤታማ መሳርያ ነው። ስለሆነም መዝሙር ወይም ሙዚቃ ግልፍተኛ ልጆችን ከማከም አኳያ ያለውን ተፅዕኖ ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ክትትል ያስፈልጋል።