የኮርስ አንድ

ሰውነታችንን ማቀፍ፡ የእርዳታ ጩኸት

ብርቱ ድምፆች


ለውጥ አምጪ የሆነውን አሰሳ በወር አበባ፣ ራስን በመቀበል እና ራስን ማወቅ ላይ ጀምሩ። የለምለምን ጉዞ ሲደግፉ፣ ትርክቶችን ሲያርሙ እና የተፈጥሮን ሃይል እና ውበት ሲቀበሉ፣የጥበብ ልጆችን ተቀላቀሏቸው ። ስለ ወር አበባ ጥልቅ ግንዛቤን አግኙና፣የተሳሳቱ አመለካከቶችን አስወግዱ፣ራስን የማወቅ እና የማብቃት ስሜትን አዳብሩ።
የኮርስ አንድ

ሰውነታችንን ማቀፍ፡ የእርዳታ ጩኸት

ብርቱ ድምፆች

ወደ ጥበብ ልጆች አለም ጎራ በሉ እና ችግሮችን ሲጋፈጡ፣ እራሳቸውን እና ሌሎችን ሲያበረታቱ ነሻጭ ጉዟቸውን አስሱ። በዚህ ኮርስ የለምለምን ህይወት የቀየረ ክስተትን ይህም የእናቷን የተሳሳቱ አመለካከቶች ለመቃወም የሚያስችል ጥንካሬ ምታገኝበትን ትመሰክራላችሁ። የፍትህን ፅናት ለወንድሟ ደህንነት ስትፋለም እና የአጎቷን ጨቋኝ ነገር ስትገዳደር ትፈትሻላችሁ። የታሪክን ሃይል ደግሞ በለምለም አያት እና በጥንድ አዛውንቶቹ የራስ ልምድ ማካፈል ውስጥ፣በወር አበባ ዙርያ የህብረተሰቡን ክልከላዎች ሲሰብሩ መስክሩ። በጋራ፣ የድንቁርና ንጣፎችን እንፈታለን እና የትምህርት እና የማስተዋል ሃይልን እንቀበላለን። የእነዚህ ደፋር ልጆች የእውነት ድል፣ የመተሳሰብ እና የማይናወጥ መንፈስን ስናከብር ይቀላቀሉን።

ኮርስ ሶስት

ኢፍትሃዊነትን መቃወም፡ ልጃገረዶችን ለለውጥ ማብቃት

Courageous Voices

የማህበረሰብ ኢፍትሃዊነትን በግንባር ቀደምትነት ሲጋፈጡ የጥበብ ልጆችን የማብቃት ጉዞ እና የመቋቋም ችሎታቸውን ይቀላቀሉ። በዚህ ኮርስ መሬታቸውን ለመጠበቅ እና ጨቋኝ ኃይሎችን ለመታገል ያላቸውን የማያወላውል ቁርጠኝነት ትመሰክራላችሁ። ሰለባ ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆነችውን እና የአፈና ሙከራን በመቃወም የቆመችውን የቦጌን ድፍረት ታሪክ አስሱ። አድካሚ የሆኑ የወሊድ ፊስቱላ ተጽዕኖዎች ቢያጋጥሟትም ለውጥ እንዲመጣ የምትደግፍ እና የሴት ልጅ ግርዛትን አደጋ በተመለከተ ግንዛቤ የምታስጨብጥ የመልካምን ነሻጭ ጽናት ትገነዘባላችሁ። ከጥበብ ልጆች ጋር በመሆን ጎጂ ልማዶችን እንዴት መቃወም እንደምትችሉ እና ለሁሉም ብሩህ የወደፊት ተስፋን መፍጠር እንደምትችሉ ትማራላችሁ ። የፍትህን ነበልባል ስናቀጣጠል፣ ሴት ልጆችን ብቁ ስናደርግ እና በማህበረሰብ ለውጥን ስናነሳሳ ተቀላቀሉን።
Created with